New "ለአብርሃም እንደ ማለ" ዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረፃድቅ | LE ABRIHAM ENDEMALE  (Official Lyrics Video)

ግጥም

ለአብርሃም እንደ ማለ

ለይስሐቅ እንደተናገረ

ለያዕቆብ እንደመሰከረ

ሕዝቡን ከሞት አሻገረ

የማለውን መሐላ ሳይረሳ ጌታ

ሕዝቡን በጽኑ ደዌ በሞት ሳይመታ

ለአባቶቻችን እንደማለላቸው

ቃሉን ፈጸመ በቃልኪዳናቸው

እግዚአብሔር በሙሴ ሕግ ባሕር ከፈለ

ከፈርዖን ሠራዊት ሕዝቡን ከለለ

እግዚአብሔር ከኖኅ ፈጸመ መሐላ

ምድር እንዳትጠፋ ከእንግዲህ በኋላ

በጥላ በልብሳቸው ድውይ ፈወሱ

ምስክሮቹ ሆነው ተመላለሱ

ጌታ ስላለ ከቅዱሳን ጋር

ሥልጣን ሰጣቸው በሰማይ በምድር

እንደ ደመና ሰፍረው በዙሪያችን

ስላሉን ምስክሮች ለነፍሳችን

እንድንማጸን በሕያው ስማቸው

አሉ በቀኙ ስላከበራቸው

New "ለአብርሃም እንደ ማለ" ዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረፃድቅ | LE ABRIHAM ENDEMALE (Official Lyrics Video)

Comments

Sign in to leave a comment

No comments yet. Be the first!

Related hymns