🔴 ከበለስ በታች ያየህኝ📍 ዘማሪ ዲያቆን ታዴዎስ ግርማ || አዲስ ዝማሬ (OFFICIAL LYRICS) #ከበለስ_በታች

ግጥም

ከበለስ በታች ያየህኝ

ሳላውቅህ አውቀህ ያሰብከኝ

ናዝራዊው ጌታ ኢየሱስ

ተመስገን የነፍሴ ንጉስ

​

መልካም ሰው አይወጣም ከናዝሬት ከተማ

ብዬ ብናገርም ስላንተ ስሰማ

በቀልን ሳታስብ የልቤን ነገርከኝ

ተንኮል የሌለበት ብለህ ተቀበልከኝ

ካለህበት ድረስ አየሁህ መጥቼ

ቀምሼ ፍቅርህን ቀረሁ ተረትቼ

ካንተ ጋር ኖራለሁ ጎድለቴ እንዲሞላ

ከእንግዲህ አልመኝም የበለሷን ጥላ

ወደፊት ተራመድኩ በመርሳት ኋላዬን

መንፈሴ ታደሰ እያየሁ ጌታዬን

ሳያቆስል ማርኮ የእሱ አድርጎኛልና

የሚበልጥ ነገር ብዙ አያለሁ ገና

በስውር ብበድል ለኃጢአት ነቅቼ

ምድረበዳ ሆንኩኝ እጅግ ተራቁቼ

ልብሴን አገኘሁ መድመቂያዪን ዛሬ

ናዝራዊውን ንጉሥ ያከብራል ከንፈሬ

🔴 ከበለስ በታች ያየህኝ📍 ዘማሪ ዲያቆን ታዴዎስ ግርማ || አዲስ ዝማሬ (OFFICIAL LYRICS) #ከበለስ_በታች

Comments

Sign in to leave a comment

No comments yet. Be the first!

Related hymns